Skip to main content

Posts

Featured

  አቶ ደመቀ መኮንን ከቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር የሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡ በውይይቱ ወቅት በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም የጋራ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል፡፡ አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በውይይት ለመፍታት ያላትን ፅኑ አቋም በተመለከተ ለቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጻ አድርገዋል፡፡ ሁለቱ ሃገራት በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት በማድነቅም የሃገራቱን ትብብር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡ የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለቱርክ ባለሃብቶች አንደኛዋ መዳረሻ መሆኗን አንስተዋል፡፡ በውይይታቸው ወቅት ሚኒስትሮቹ ሃገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት በማስታወስ፥ አጋርነታቸውን በተለያዩ ዘርፎች ማሳደግ እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ሚኒስትሮቹ ከውይይታቸው ባሻገር ኢትዮጵያ እና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ አመት በጋራ ያከበሩ ሲሆን፥ በአንካራ አዲስ የተገነባው የኢትዮጵያ ኤምባሲም መርቀው ከፍተዋል፡፡

Latest Posts